|
የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር ዘመቻ ደመላሽ ህዝባዊ የድጋፍ ጥሪ! የተከበራችሁ በመላው አለም የምትገኙ ኢትዮጵያውያን ወንድሞቻችንና እህቶቻችን በሙሉ እኛ የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር ሰራዊት አባላት በሃገራችን የተንሰራፋውን ጸረ ህዝብና ዘረኛ ስርዓት በመፋለም ለአመታት ትዳር ልጅ ቤት ንብረት ሳንል በየበረሃው በየዱር ገደሉና ሸንተረሩ መስዋዕትነትን በመክፈል ላይ መሆናችን ለናንተ የተሰወረ አይደለም። በሰፊው በተንቀሳቀስንባቸው የሃገሪቱ ሰሜናዊ ክፍሎች የህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይን የግድያ ሰራዊት አደባይተነዋል : ልዩ የስለላና የግድያ ታጣቂዎችንም ዳግም እንዳይመለሱ በማድረግ ቀጥተናቸዋል። ዘረኛው ስራት የሃገሪቱን አንጡራ ሃብት ወደውጭ የሚያግዋጉዝበትን የኢትዮ- ሱዳን መንገድ በማጠር ዝርፊያውን ገተነዋል አሊያም በብርጌድ ጦር ታጅቦ እንዲሄድ አስገድደነዋል። እኛ የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር ተዋጊዎች አላማችን አንድና አንድ ነው። ዛሬ በህዝባችን ትከሻ ላይ በተለያየ ዘዴ ተቀምጦ በማን አለብኝነት ለሃያ አመታት የሚገድለውን የሚያስረውን የሚያሰቃየውንና የሚያሳድደውን ዘረኛ የገዳዮች ስብስብ በሃይል ለመጣልና በሃገራችን ላይ ህዝባዊና ዴሞክራሲያዊ ስርዓት እስከሚቆም ድረስ የህዝብ ዘበኛ ሆኖ ማገልገል ነው። የሃገር ዳር ድንበር ሲገሰስ ። የህዝብ ባህልና ስራት ሲፈርስ ። የዜጎች ደም ሲፈስ የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር ዘብ ይቆማል ይፋለማል። ገዳዮቹንና በላኤ ሰቦችንም ይበቀላል በህይወት እስካሉም ድረስ እያሳደደ ለፍርድ ያቀርባል። የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር ተዋጊዎች በወልቃይት ጸገዴና ጠለምት፣, በአርባ ጉጉና በበደኖ። እንዲሁም በጋምቤላ ህዝቦቻችን ላይ የደረሰው ጅምላ ፍጅት እንዲሁም የዘር ማጥፋት ግፍ እንደ እግር እሳት ያቃጥለናል፤ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ኢ-ሰብዓዊ ግድያ ያንገበግበናል፤ ከምርጫ 97 ጋር በተያያዘም በመላው ሃገሪቱ የተካሄደው ግፍና ጭፍጨፋ ዛሬም ድረስ እንቅልፍ ይነሳናል። በየገጠሩና በየመሃል ሃገሩ በተናጠል እየታደኑ የሚታሰሩት የሚገደሉትና የሚሰወሩት ወገኖቻችን ህይወት ያሳዝነናል። የሃገሪቱ ብርቅዬ ልጆች እየተመነጠሩ ለእስር ሲዳረጉና ሰቆቃ ሲፈጸምባቸው ስናይ እልክ ይተናነቀናል። ዛሬም የፍትህ ያለ በሚል አንጀታቸው ጭምር እያለቀሰ የሚገኙትና የሙታን ሰማእታቱ እርዳታ የጎደለባቸው እናቶች አባቶች እንዲሁም መላ ቤተሰቦች የልጆቻቸው ደም ደመ ከልብ ሆኖ የመቅረቱን ያህል እንደሚሰማቸው ይታወቀናል።:: |