company logo

የራዲዮ ፕሮግራም

Link

 

 





picture 167.jpg

የእርሶ ምርጫ

የወደፊት የኢትዮጵያን ዕድል የሚወሰነው?
 
picture 215.jpg

Login Form



Content View Hits : 52009
17-05-2004
 
15-05-2004
 
የዘመቻ ደምመላሽ

የኢሕአግ የዘመቻ ደምመላሽ ሠራዊት ወታደራዊ ጥቃት እየተፋፋመ ይገኛል፣

   የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር የዘመቻ ደምመላሽ ሰራዊት በሰሜን ጎንደር ላይ አርማጭሆ ዶጋው ልዩ ስሙ ጉርማጭት በተባለ አካባቢ ላይ በታህሳስ 21- 2004 ዓ.ም በመቶ አለቃ ገበየሁ የሚመራው ልዩ ሃይል ጋር በተካሄደ ውጊያ 9 የወያኔ ልዩ ሃይል ታጣቂዎች በመግደልና 16 በማቁሰል ከባድና ቀላል መሳሪያዎችን ከነ መሰል ጥይቶቻቸው ጋር መማረኩን የኢሕአግ ወታደራዊ መምሪያ ከስፍራው አስታወቀ፣

  የኢሕአግ ወታደራዊ መምሪያ ጨምሮ እንደገለፀው፦ በአካባቢው ( በስፍራው) የዘመቻ ደምመላሽ ሰራዊት በተከታታይ እያካሄደ የሚገኘው ድንገተኛ ወታደራዊ ማጥቃት እርምጃ በወያኔ የመከላከያ ፤ የሚሊሻና የልዩ ሃይል…. ታጣቂዎች ዘንድ የውጊያ ሞራል መላሸቅ እና የአርበኛው የጀግንነት በትር የአገዛዙን ታጣቂዎች አንገት የሚያስደፋ ሆኖ መገኘቱን ለአገዛዙ ቅልብ ጦር ቅርበት ያላቸው ወገኖች ገለፁ፣

Read more...
 
ዘመቻ ደምመላሽ በወልቃይት ጥቃት ፈፀመ

የዘመቻ ደምመላሽ የኢህአግ ሠራዊት በሰሜን ጐንደር ወልቃይት ልዩ ስሙ ሶረቃ በተባለ ቦታ ወታደራዊ ጥቃት ፈፀመ።።

  የዘመቻ ደምመላሽ የኢህአግ ሰራዊት የታጠቀ ሀይሉን መከታ አድርጐ ህዝብን እያወደመ የሚገኘውን የወያኔ ቡድን ፊት ለፊት በመጋፈጥና አይቀጡ ቅጣት በመቅጣት በኢትዮጵያ ህዝብ ዘንድ ያለውን ጥልቅ ፍቅር በተግባር የተደገፈ ተጋድሎ በማካሄድ የዘመቻ ደምመላሽ የኢህአግ ሠራዊት የወገን ደራሽ መሆኑን በተከታታይ በሚያደርገው እልህ አሥጨራሽ የፀረ-ወያኔ ፍልሚያ በማስመስከር ላይ ይገኛል።።

Read more...
 
ዘመቻ ደመላሽ ወታደራዊ ጥቃቱን ቀጥሏል

   የዘመቻ ደምመላሽ የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሠራዊት በሰሜን ጎንደር ላይ አርማጭሆ ልዩ ስሙ አሸሬ በተባለ ቦታ ጥቃት ፈፀመ፣

   የዘመቻ ደምመላሽ የኢህአግ ሠራዊት ከወያኔ ቅጥረኛና ምንደኛ የመከላከያና የልዩ ሃይል ቡድን ጋር የጀመረውን የማጥቃት ዘመቻ ከመቸውም ጊዜ በላይ አጠናክሮ በመቀጠል ሕዳር 13 ቀን 2004 ዓ.ም በሰሜን ጎንደር ላይ አርማጭሆ ልዩ ስሙ አሸሬ በተባለ ቦታ ባደረገው እልህ አስጨራሽ ውጊያ በጠላት ላይ ከፍተኛ ኪሳራ በማድረስ አኩሪ የሆነ ወታደራዊ ድል መጨበጡ ታወቀ፣

Read more...
 
ዘመቻ ደምመላሽ ወታደራዊ ጥቃት ፈጸመ

የዘመቻ ደምመላሽ አካል የሆነው የኢሕአግ ሠራዊት  ወታደራዊ ጥቃት ተጠናክሮ ቀጥሏል፣

   ከወራት በፊት የተጀመረው የዘመቻ ደምመላሽ ሁሉ አቀፍ የወታደራዊ፤ የፖለቲካ፤ የማደራጀት፤ የዲፕሎማሲ እንዲሁም የፕሮፓጋንዳ አገርና ሕዝብ የመታደግ ታሪካዊና አኩሪ ተጋድሎ አንዱና ዋነኛው የወታደራዊ ማጥቃት እየተፋፋመ ይገኛል፣ በህዳር 6-2004 ዓ.ም በሰሜን ጎንደር አርማጭሆ ልዩ ስሙ ስናር በሚባል አካባቢ የዘመቻ ደምመላሽ ስያሜ አንግቦ እየተንቀሳቀሰ የሚገኘው የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር /ኢሕአግ/ ሰራዊት ወያኔው በአዲስ መልክ ያደራጀው ልዩ ሃይል የተሰኘው ታጣቂ ሃይል ጋር በተካሄደ ውጊያ 6 ገድሎ 12 ያቆሰለ ሲሆን፦ 7 ክላሽንኮፍ ጠበንጃ ከነ መሰል ጥይቶቹ ጋር የግሉ አድርጓል፣

Read more...
 
መግለጫ

ከኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር /ኢሕአግ/

የተሰጠ መግለጫ

 

   በፀረ- ሽብርተኝነት ካባ ሕዝብን እያሸበሩ መኖር አይቻልም!

   

   አገራችን ኢትዮጵያን በማን አለብኝነትና በእብሪተኝነት በውስን ግለሰቦች የጥፋት ጭንቅላት በብርቱ መሰቃየት ከጀመረች የአንድ ወጣት እድሜ ተቆጥሯል፣ አገዛዙ የእብሪት ጡንቻውን በአገሬው ላይ ማሳረፍ የጀመረው ገና የሚኒልክ ቤተ-መንግስት እንደገባ ነበር፣ የኢትዮጵያ ሕዝብም የትምክህተኛውን ቡድን የፀረ- አገርና የፀረ-ሕዝብ ዳንኬራ አይቶ እንዳላየ ሰምቶ እንዳልሰማ ዝም ብሎ የተመለከተበት አንድም ጊዜ አልነበረም፣

Read more...
 
ዘመቻ ደመላሽ

የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር ዘመቻ ደመላሽ ህዝባዊ የድጋፍ ጥሪ!

የተከበራችሁ በመላው አለም የምትገኙ ኢትዮጵያውያን ወንድሞቻችንና እህቶቻችን በሙሉ

እኛ የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር ሰራዊት አባላት በሃገራችን የተንሰራፋውን ረ ህዝብ ዘረ ስርዓት በመፋለም ለአመታት ትዳር ልጅ  ቤት ንብረት ሳንል በየበረሃው በየዱር  ገደሉና ሸንተረሩ መስዋዕትነትን በመክፈል ላይ መሆናችን ለናንተ የተሰወረ አይደለም።

በሰፊው በተንቀሳቀስንባቸው የሃገሪቱ ሰሜናዊ ክፍሎች የህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይን የግድያ ሰራዊት አደባይተነዋል  : ልዩ የስለላና የግድያ ታጣቂዎችንም ዳግም እንዳይመለሱ በማድረግ ቀጥተናቸዋል። ዘረኛው ስራት የሃገሪቱን አንጡራ ሃብት ወደውጭ የሚያግዋጉዝበትን የኢትዮ- ሱዳን መንገድ በማጠር ዝርፊያውን ገተነዋል አሊያም በብርጌድ ጦር ታጅቦ እንዲሄድ አስገድደነዋል።

እኛ የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር ተዋጊዎች አላማችን አንድና አንድ ነው። ዛ በህዝባችን ትከሻ ላይ በተለያየ ዘዴ ተቀምጦ በማን አለብነት ለሃያ አመታት የሚገድለውን የሚያስረውን የሚያሰቃየውንና የሚያሳድደውን ዘረኛ የገዳዮች ስብስብ በሃይል ለመጣልና በሃገራችን ላይ ህዝባዊና ዴሞክራሲያዊ ስርዓት እስከሚቆም ድረስ የህዝብ ዘበኛ ሆኖ ማገልገል ነው።

 የሃገር ዳር ድንበር ሲገሰስ ። የህዝብ ባህልና ስራት ሲፈርስ ። የዜጎች ደም ሲፈስ የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር ዘብ ይቆማል ይፋለማል። ገዳዮቹንና በላኤ ሰቦችንም ይበቀላል በህይወት እስካሉም ድረስ እያሳደደ ለፍርድ ያቀርባል።

የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር ተዋጊዎች በወልቃት ጸገዴና ጠለምት፣, በአርባ ጉጉና በበደኖ። እንዲሁም በጋምቤላ ህዝቦቻችን ላይ የደረሰው ጅምላ ፍጅት እንዲሁም የዘር ማጥፋት ግፍ እንደ እግር እሳት ያቃጥለናል፤ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ኢ-ሰብዓዊ ግድያ ያንገበግበናል፤ ከምርጫ 97 ጋር በተያያዘም በመላው ሃገሪቱ የተካሄደው ግፍና ጭፍጨፋ ዛሬም ድረስ እንቅልፍ ይነሳናል። በየገጠሩና በየመሃል ሃገሩ በተናጠል እየታደኑ የሚታሰሩት የሚገደሉትና የሚሰወሩት ወገኖቻችን ህይወት ያሳዝነናል።

የሃገሪቱ ብርቅዬ ልጆች እየተመነጠሩ ለእስር ሲዳረጉና ሰቆቃ ሲፈጸምባቸው ስናይ እልክ ይተናነቀናል።

ዛሬም የፍትህ ያለ በሚል አንጀታቸው ጭምር እያለቀሰ የሚገኙትና የሙታን ሰማእታቱ እርዳታ የጎደለባቸው እናቶች አባቶች  እንዲሁም መላ ቤተሰቦች የልጆቻቸው ደም ደመ ከልብ ሆኖ የመቅረቱን ያህል እንደሚሰማቸው ይታወቀናል።::

Read more...
 
መግለጫ

የአባላት ስምምነት የትግላችን መሰረት ነው

ከኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር የተሰጠ መግለጫ

 

የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር ባሳለፋቸው ጸረ ወያኔ ትንቅንቅ አመታት ትግሉን የበለጠ አታካች አርጎት የቆየው በድርጅቱ ውስጥ ይታይ የነበረው የርስ በርስ ትርምስ እንደነበረ ጸሃይ የሞቀው ሃቅ ነው።

ምንም እንኳን ወያኔ ሰራሽ የሆኑትን ስልታዊ አፍራሽ እንቅስቃሴዎች ጥርሳችን ነክሰን ስንጋፈጣቸውና ስናሸንፋቸው የቆየን ቢሆንም አብረውን ሆነው ነገር ግን የድርጅታችንን ህልውና በሚፈታተን መልኩ ካወኩን የራስችን አርበኖች ጋር ያደረግነውም የርስበርስ ሽኩቻ እንዲህ ቀለል አርገን የምናያቸው አይሆኑም።

Read more...
 
የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ታጋዮች በወያኔ መደለያ አይንበረከኩም-- ያዳምጡ
 


Copy right @2010 arbegnochginbar